በማያንማር በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ 255 ኢትዮጰያዉያን ወደ ታይላንድ ለመግባት እየተጠባበቁ እንደሆነ ለኢትዮ ኤፍኤም ተናግረዋል።
በትላንትናው ዕለትም ወደ ታይላንድ ትሄዳላችሁ ተብለው ጉዟቸውን እየተጠባበቁ ከሚገኙት መካከል 30ዎቹ ሴቶች፤ 225ቱ ደግሞ ወንዶች መሆናቸዉ ታውቋል።
በማያንማርና እና በታይላንድ ማጎሪያ ካምፕ ዉስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያዉያን ስደተኞች ከፍተኛ ስጋት ላይ መሆናቸዉን በተደጋጋሚ ለጣቢያችን ቅሬታ እያቀረቡ ይገኛሉ።
አሁንም ቢሆን መንግስት በስፍራዉ ስላሉ ኢትዮጵያዉያን ምላሹን እንዲሰጥ እና ወደ ሀገራቸው እንዲመልሳቸው ጠይቀዋል፡፡
ሊዲያ ደሳለኝ
መጋቢት 23 ቀን 2017 ዓ.ም
