ሃንጋሪ ከአለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ልትወጣ ነው።

የሃንጋሪ መንግስት ከአለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት (ICC) አባልነት እራሱን ማግለሉን አስታወቀ።

እርምጃው በጠቅላይ ሚኒስትር ቪክቶር ኦርባን መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣን ይፋ የተደረገው በአይሲሲ የእስር ማዘዣ የወጣባቸው የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታኒያሁ ለሀገር ጉብኝት ሃንጋሪ ከገቡ ከሰዓታት በኋላ ነው።

ኦርባን የፍርድ ማዘዣው እንደወጣ ባለፈው ህዳር ወር ኔታንያሁን ጋብዘዋቸው የነበረው ውሳኔው በሃገራቸው ላይ “ምንም ተጽእኖ አይኖረውም” በማለት ነበር።

በህዳር ወር ላይ የአይሲሲ ዳኞች ኔታንያሁ በጋዛ በጦርነት በሰው ልጆች ላይ ለተፈጸሙ ወንጀሎች ተጠያቂ ናቸው ብለው ነበር፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ የአይሲሲን ውሳኔ “ፀረ-ሴማዊ” ሲሉ ማውገዛቸውን አስታውሱ የዘገበው ቢቢሲ ነው፡፡

መጋቢት 25 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *