የሰቆጣ ቃልኪዳን ትግበራ በወረዳ ቁጥር ላይ ብቻ መገምገም አይገባዉም ተባለ

የምግብና ስርዓተ ምግብ የሚኒስትሮች ስትሪንግ ኮሚቴ አድርጎት በነበረዉ ስብሰባ ነዉ ይህ የተባለዉ።

ግብርና ሚኒሰትር በ 2018 አ.ም በጀት አመት የሰቆጣ ቃልኪዳን ስምምነት ትግበራን 186 ወረዳዎች ላይ ተደራሽ ለማድረግ እቅድ መያዙን ተናግሯል።

ይህንን ተከትሎ የኮሚቴው አባል የሆኑት ኘሮፊሰር ብርሃኑ ነጋ “የቃልኪዳኑ ትግበራ ሲጀመር ከነበሩት ወረዳዎች ምን ያህሉ ራሳቸዉን ችለዉ ወጡ?” የሚለዉን መመለስ ያስፈልጋል ብለዋል።

አያይዘዉም “ይህንን መመለስ ካልተቻለ የወረዳዎቹን ቁጥር በማሳደግ ተደራሽ ለመሆን መጣር የድክመት እንጂ የስኬት ደረጃ መሆን አይገባም” ሲሉ ተናግረዋል።

የግብርና ሚኒሰትሩ ዶ/ር ግርማ አመንቴ በኢትዮጵያ ያለዉን የመቀንጨር ምጣኔ ለመቀነስ እንጂ የወረዳዎቹን ቁጥር ለማሳደግ እየተሞከረ ያለዉ በቁጥር ለመገምገም አይደለም ሲሉ ምላሽ ሰተዋል።

የምግብ ዋስትና ዉስብስብ ችግሮች ዉስጥ አደጋ ላይ ለመሆኑ ማሳያዉ የመቀንጨር ምጣኔ አንዱ ነዉ።

በኢትዮጵያ የመቀንጨር ምጣኔን 30 በመቶ ማድረስ ተችሏል ያሉት የግብርና ሚኒስትሩ በዚህም እየቀነሰ መቷል ቀሪ ስራዎች ግን አሉ ብለዋል ።

በስብሰባዉ በተለይም በሰቆጣ ቃልኪዳን የታቀፉ ወረዳዎች ራሳቸዉን ችለዉ እንዲቆሙ ለማድረግ የሚያስችል ሁኔታዎች ሊፈጠሩ ይገባል የሚል ሀሳብ ከኮሚቴ አባላት ተነስቷል።

የግብርና ሚኒስትር በቀጣዩ በጀት አመት ይህ የቃልኪዳን ስምምነት ይተገበርባቸዋል በተባሉ ወረዳዎች ላይ ክልሎች በጀት መድበዉ እየሰሩ ነዉ ብሏል።

የሰቆጣ ቃልኪዳን ከ 7.8 ሚሊየን በላይ የሆኑ ህጻናትን እስከ 2022 ዓ/ም ድረስ ከመቀንጨር በመታደግ ሙሉ እድገታቸው ተመጣጣኝ እንዲሆን ለማድረግ ቃል የተገባበት ስምምነት ነዉ።

ከ 4 አመታት በፊት የተዘጋጀዉን የስርአተ ምግብ ፍኖተ ካርታ አስራ አምስት ሚኒስትር መ/ቤቶችን ያቀፈዉ ኮሚቴ እያስተባበረዉ ይገኛል ተብሏል።

ቁምነገር አየለ

መጋቢት 25 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *