በአገራችን አንድ የድንገተኛ ህክምና ሀኪም ከግማሽ ሚሊየን እስከ 1 ሚሊየን ለሚደርስ ታካሚ አገልግሎት ይሰጣል።

በድንገተኛ ህክምና የማስተርስ ነርስ ያለው ባለሙያ ደግሞ ለግማሽ ሚሊየን ህዝብ አገልግሎት ለመስጠት ይገደዳል።

በአገራችን ያለው የድንገተኛ ህክምና ባለሙያዎች ቁጥር ከማህበረሰቡ ጋር የተጣጣመ አይደለም ተብሏል።

ከጣቢያችን ጋር ቆይታ ያደረጉት የኢትዮጵያ ድንገተኛ እና ፅኑ ህክምና ባለሙያዎች ማህበር ፕሬዝዳንት ዶክተር ወልደሰንበት ዋጋኖ፤በዓለም ጤና ድርጅት መስፈርት 1 ነርስ ወይም ሀኪም ለ50ሺህ እና ከዛ በታች ላለ ታካሚ መድረስ አለበት።

በእኛ አገር ያለው ሁኔታ ግን ከዚህ በተቃራኒ መሆኑን ይገልፃሉ።

በድንገተኛ ህክምና ዘርፍ 2መቶ1 ስፔሻሊስት ሀኪሞች እና 2መቶ50 ማስተርስ እና ፒኤችዲ ያላቸው ነርሶች መኖራቸውን ነግረውናል።

በጎ ፍቃደኞችን ጨምሮ 500 ፓራሜዲክ አሉ ያሉት ፕሬዝዳንቱ፤ በአጠቃላይ ወደ 7መቶ50 ባለሙያዎች አሉን ብለዋል።

ድንገተኛ ህክምና በአገራችን እውቅና ከተሰጠው 10 ዓመት ሆኖታል የሚሉት ዶ/ር ወልደሰንበት፤ በ10 ዓመት ዕድሜ አሁን ያለበት ደረጃ እንደ አገር መልካም ውጤት ነው ይላሉ።

ነገርግን ማህበረሰቡ ከሚፈልገው፣ካሉት አደጋዎች ብዛት እና ከአገሪቱ ዕድገት አንፃር እንደ አገር ብዙ የሰው ሀይል ያስፈልገናል ብለዋል።

ይህን ችግር ለመቅረፍ ከጤና ሚኒስቴር ጋር በጋራ በመሆን በተለያዩ የህክምና ዘርፍ ለተማሩ እና ለሚሰሩ ባለሙያዎች አጫጭር ስልጠናዎችን እየሰጠን እንገኛለን ብለውናል።

እስከዳር ግርማ

መጋቢት 26 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *