ትራምፕ ኢራን ከአሜሪካ ጋር በቀጥታ መነጋገር እንደምትፈልግ “አስባለሁ” አሉ።

ዶናልድ ትራምፕ ኢራን ከአሜሪካ ጋር በቀጥታ ለመነጋገር “ልትስማማ” እንደምትችል ጠቁመዋል።

የዩኤስ ፕሬዝዳንት ሐሙስ ዕለት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ አስተዳደራቸው ከቴህራን ጋር የፊት ለፊት ዲፕሎማሲ የመፍጠር ተስፋ ያለው ይመስላል ይላል የአልጀዚራ ዘገባ፡፡

“ቀጥተኛ ንግግሮች ቢሆኑ የተሻለ ይመስለኛል” ብለዋል ትራምፕ “በፍጥነት ይሄዳል ብዬ አስባለሁ፣ ኢራናዊያን አሸማጋዩቸን ፈልገው ነበር ፡፡ይህ ከአሁን በኃላ ይሆናል ብዬ አልገምትም” ብለዋል ትራምፕ፡፡

ባለፈው ወር የትራምፕ አስተዳደር የኢራንን የኒውክሌር መርሃ ግብር በተመለከተ ድርድር እንዲደረግ ለኢራን መንግስት ደብዳቤ መላኩ የሚታወስ ነው። ይህ ካልሆነ ግን አሜሪካ በኢራን ላይ ወታደራዊ ጥቃቶችን እንደምፈጽም በጊዜው ሲያስፈራሩ ነበር።

ቴህራን ከዚህ ቀደም ከዋሽንግተን ጋር ቀጥተኛ ውይይትን ውድቅ አድርጋለች፡፡
ይሆን እንጂ ተዘዋዋሪ ድርድርን ግን ክፍት እንደሆነ ተናግራለች።

ኢራን በእርግጥ አቋሟን ቀይራ ወይም ትረምፕ ስለ ቴህራን አቋም እየገመቱ እንደሆነ ግልጽ አይደለም ብሏል አልጀዚራ በዘገባው።

የዩናይትድ ስቴትስ አስተዳደር የሀገሪቱን በተለይም ወደ ቻይና የምትልከውን የነዳጅ ዘይት ሙሉ በሙሉ ለማፈን በማለም በኢራን ላይ ማዕቀብ ሲከማች ቆይቷል።

መጋቢት 26 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *