ከኦንላይን የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎቶች 1.45 ቢሊየን ብር ገቢ ተገኘ

ባለፋት ዘጠኝ ወራት በሀገር አቀፍ ደረጃ ከ2 ሚሊየን 600 ሺህ በላይ የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎቶችን በኦን ላይን በመስጠት 1.45 ቢሊዮን ብር መገኘቱ ተገለፀ።

ይህ የተገለጸዉ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የሚኒስትር መስሪያ ቤቱንና የተጠሪ ተቋማትን የዘጠኝ ወራት የዘርፍ እቅድ አፈፃፀም ግምገማ ከአመራሮች ጋር በዛሬው እለት እያካሄደ ባለበት ወቅት ነዉ።

የንግድ ስርዓትና ላይሰንሲንግ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር አብዱልሃኪም ሙሉ ባለፋት ዘጠኝ ወራት በሀገር አቀፍ ደረጃ 2 ሚሊዮን 5መቶ72ሺህ109 የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎቶችን በኦን ላይን ለመስጠት ታቅዶ 2ሚሊዮን 6መቶ16 ሺህ 506 የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎቶችን በኦን ላይን መሰጠቱን ገልፀዋል።

ዶ/ር አብዱልሃኪም ከእቅድ አንፃር 102 በመቶ ማሳካት እንደተቻለ አንስተዋል።

አፈፃፀሙ ከባለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ722 ሺህ 246 ወይም 38.2 በመቶ ብልጫ እንዳለው የገለፁት ሚኒስትር ዴኤታው ከገቢ አንፃርም ባለፋት ዘጠኝ ወራት ከተሰጡ የኦንላይን የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎቶች 1.45 ቢሊየን ብር ገቢ የተሰበሰበ መሆኑን ጠቅሰዋል።

የተገኘው ገቢ ከባለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ9.02 ሚሊየን ብር ወይን 166.2 በመቶ ብልጫ እንዳለው ሚኒስትር ዴኤታው ገልፀዋል።

ልኡል ወልዴ

ሚያዚያ 01ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *