በአማራ ክልል የምክክር ሂደት የህብረተሰብ ወኪሎች መሰረታዊ አጀንዳዎችን ለይተዋል ሲል ኮሚሽኑ አስታውቋል።
በአማራ ክልል ባህርዳር ከተማ ባሳለፍነው ቅዳሜ መጋቢት 27 ጅማሮውን ባደረገው የምክክር መድረክ ላይ የህብረተሰብ ወኪሎች አጀንዳቸውን ለይተዋል ተብሏል።
ተሳታፊዎቹ እንደ አጀንዳ እንዲያዝላቸው ያነሷቸው ጉዳዮች በነፃነት የመንቀሳቀስ፣ ተንቀሳቅሶም ኢኮኖሚያዊ ገቢ የማግኘት መብት፣ የህገ-መንግስት መሻሻል፣ የወሰንና ማንነት ጥያቄዎች፣ እንዲሁም የክልሉ ሰላም፣ ጸጥታና ደህንነት ጉዳዮች እንደሚገኙበት ተገልጿል፡፡
ተሳታፊዎቹ አሁንም ቢሆን የሀይል አማራጮችን መጠቀም መፍትሄ አይሆንም የሚል አጀንዳን አቅርበናል ያሉ ሲሆን፤ መንግስት የሚጠበቅበትን ሀላፊነት በመወጣት የሚዋጡ ሃሳቦችን ዳር እንዲያደርስ ሲሉ ጠይቀዋል።
የክልሉ የምክክር ሂደት አስባባሪ ኮሚሽነር መላኩ ወ/ማርያም ላለፉት አምስት ቀናት ሲካሄድ የቆየው የህብረተሰብ ወኪሎች ምክክር መጠናቀቁን ገልፀዋል፡፡
ኮሚሽር መላኩ ወ/ማርያም በዚህ ወቅት እንደተናገሩት ባለፉት አምስት ቀናት በተካሄደው የህብረተሰብ ወኪሎች ምክክር ከክልሉ 263 ወረዳዎች የመጡ ከ4ሺ 500 በላይ ወኪሎች ተሳትፈዋል፡፡
ሂደቱ አሳታፊ፣ አካታችና ግልፅ በሆነ ሁኔታ ተካሂዶ ተጠናቋል በማለትም ኮሚሽነሩ ተናግዋል፡፡
ተሳታፊዎች ለክልላቸውና ለሀገራቸው ጠቃሚ የሆኑ እጅግ መሰረታዊ ሃሳቦችን በውይይት አዳብረው መለየታቸውንም በነበረን ክትትልና ድጋፍ ተመልክተናል ሲሉም ገልፀዋል።
ለዓለም አሰፋ
ሚያዚያ 2 ቀን 2017 ዓ.ም
