በአገራችን ተላላፊ ያልሆኑ ህመሞች አደጋን ጨምሮ ከ51 በመቶ በላይ የሞት መንስኤ መሆናቸው ተገለፀ።

ከዚህ ቀደም ተላላፊ የሆኑ እንደ ቲቢ እና ኢንፌክሽን ያሉ ህመሞች ገዳይ እንደሆኑ ይነገር ነበር፡፡

አሁን ላይ ግን በኢትዮጵያ ከሚከሰተው ሞት ተላላፊ ያልሆኑ ህመሞች አደጋን ጨምሮ ከ51 በመቶ በላይ ድርሻ አላቸው ሲል ጤና ሚኒስቴር ለኢትዮ ኤፍኤም አስታውቋል።

በጤና ሚኒስቴር ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች እና የአዕምሮ ጤና ዴስክ ሀላፊ ዶክተር ሰላማዊት አየለ፤የከተሜነት መስፋፋት፣ የአልኮልና የሲጋራ ተጠቃሚነት ለዚህ ቁጥር መብዛት እንደምክንያት እንደሚቀመጥ ነግረውናል።

መድኃኒቶችን በማቅረብ እንዲሁም በመድኃኒት አቅርቦት ዙሪያ የሚሰሩ የግልና የመንግስት አካላትን በማሰባሰብ የጤና ሚኒስቴር እየሰራ እንደሆነ የገለፁት ሃላፊዋ፤ከፍላጎቱ አንፃር አቅርቦቱ ላይ እጥረት እያጋጠመ ነው ብለዋል፡፡

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ተላላፊ ባልሆኑ ህመሞች ዙሪያ ትኩረት አድርጎ እየሰራ እንደሆነ ጠቅሰው፤ ማህበረሰብ ላይ ግንዛቤን መፍጠር ላይ ትኩረት ተደርጎ እየተሰራ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

አፎሚያ አሸናፊ

ሚያዚያ 06 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *