የግንባታ ማእድናቱን የዋጋ ተመን ማስተካከያ እየተደረገበት መሆኑንም ሰምተናል።
ከ2015 አመት ጀምሮ በጋምቤላ ክልል ሁሉም ወረዳዎች ላይ የግንባታ ማእድናት ከፍተኛ ዋጋ እየተጠየቀባቸዉ ነዉ ተብሏል።
ለዋጋ ጭማሪዉ ምክንያት ሆኗል የተባለዉ የነዳጅ ዋጋ መጨመር እንደሆነ የክልሉ የማእድን ሀብት ልማት ቢሮ ገልፆል።
በቢሮዉ ሀላፊ የሆኑት አቶ ኡጅሉ ጊሎ ይህንን የማእድናቱ የተጋነነ የዋጋ ጭማሪ ተከትሎ አቤቱታ መቅረቡን ገልፀዋል።
የዋጋ ንረቱን ለመቆጣጠር እንዲቻል ጥረት እየተደረገ ነዉ ÷ በተጋነነ ዋጋ ሲሸጥ የነበረዉን የማእድናቱን ዋጋ ማስተካከያ አድርገናል ብለዋል ሀላፊዉ።
በዚህም በኬላዎች ይጣል የነበረዉን የቀረጥ እና ኮቴ ዋጋ ማስተካከያ እንደተደረገ ቢሮዉ ማሳወቁን ከክልሉ የተገኘዉ መረጃ አመላክቷል።
ምክንያታዊ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ እንዳይኖር እና ማስተካከያ በተደረገበት የዋጋ ተመን እንዲሸጥ ማሳሰቢያ መሰጠቱን ገልፆል።
ቢሮዉ የዋጋ ማሻሻያዉ ያደረኩት ይመለከታቸዋል ከተባሉ የባለድርሻ አካላት ጋር ባደረጉት ንግግር ነዉ ብሏል።
ቁምነገር አየለ
ሚያዚያ 7 ቀን 2017 ዓ.ም
