ምክር ቤቱ የመገናኛ ብዙኃን አዋጅን ለማሻሻል የቀረበ ረቂቅ አዋጅን ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል‼️

6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 25ኛ መደበኛ ስብሰባ ነገ ይካሄዳል።

ምክር ቤቱ በ25ኛ መደበኛ ስብሰባው የመገናኛ ብዙኃን አዋጅን ለማሻሻል የቀረበ ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ የዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚያቀርበውን ሪፖርት እና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ አዋጁን እንደሚያፀድቅ ይጠበቃል።

በተጨማሪም የተቀናጀ የውኃ ሀብት አስተዳደር ማስፈጸሚያ የተፋሰሶች ከፍተኛ ምክር ቤት ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ የውኃ፣ መስኖ እና ቆላማ አካባቢዎች እና አካባቢ ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚያቀርበውን ሪፖርት እና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ አዋጁን ያፀድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅም ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ሚያዚያ 8 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *