የኢትዮጵያ መገለጫ የሆነውን ዋልያ በቡድን ተደራጅተው እያደኑ ሲያርዱ የነበሩ ግለሰቦች በጃናሞራ ወረዳ አስተዳደር የጸጥታ አካላትና በስሜን ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ ጽ/ቤት ሬንጀሮች ትብብር በቁጥጥር ስር መዋላቸው ታውቋል።
ቧሂት ተብሎ በሚጠራው የፓርኩ ክፍል በተደረገ ቅኝት፤ ሁለት ዋልያ በጥይት በመግደል አርደው በአህያ እየጫኑ እያለ ተደርሶባቸው በተደረገ የተኩስ ልውውጥ ሁለቱ በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን፤ ቀሪዎቹን ወንጀለኞች ወደ ህግ ለማቅረብ የጸጥታ ሀይሉ በስምሪት ላይ እንደሚገኝ ፓርኩ አስታውቋል።
በህግ ቁጥጥር ስር ያሉት ወንጀለኞች ላይ የወረዳው ፖሊስ ጽ/ቤት የምርመራ ስራውን እያካሄደ ነው ተብሏል።
በስሜን ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ የሚገኘው ዋልያ በተለያዩ ምክንያቶች ቁጥሩ መቀነሱን መዘገባችን ይታወሳል።
ሚያዚያ 9 ቀን 2017 ዓ.ም
