የጸሎተ ሐሙስ ሥነ-ሥርዓት እና ህፅበተ እግር በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን መንበረ ጸባዖት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል እየተከናወነ ነው፡፡
በሥነ-ሥርዓቱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስን ጨምሮ ሊቃነ ጳጳሳት፣ ቀሳውስትና ምዕመናን ተገኝተዋል።
የእምነቱ ተከታዮች ኢየሱስ ክርስቶስ ዝቅ ብሎ ለሓዋርያቱ ያሳየውን ትሕትና በሕይወታቸው ሊገልጡት እንደሚገባ ተገልጿል፡፡
ጸሎተ ሀሙስ ኢየሱስ ክርስቶስ ዝቅ ብሎ የሓዋርያቱን እግር ያጠበበት እና ትሕትናን ያስተማረበት ዕለት ነው።
ሚያዚያ 9 ቀን 2017 ዓ.ም
