በክልሉ የህዝብ ጥያቄዎች በአግባቡ አመራሩ መልስ ሊሰጣቸዉ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
የኦሮሚያ ክልል የዘጠኝ ወራት የስራ አፈፃፀም ግምገማን በአዳማ ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል።
የክልሉ ኘሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ የህዝብ የልማት እና የአገልግሎት ጥያቄዎች ለመመለስ አመራር ላይ ለሚገኙ አካላት ማሳሰቢያ ሰጥተዋል።
አሁን ላይ ከህዝብ እየተነሳ ያለዉን የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ምላሽ በመስጠት አመራሮች ሀላፊነታቸዉን በአግባቡ ይወጡ ብለዋል።
ኘሬዝዳንቱ በመድረኩ የዘጠኝ ወራቱን ግምገማ በክልሉ ላይ የሚስተዋሉ እና የታዩ ክፍተቶችን በአግባቡ ለመፈተሽ ነዉ ብለዋል።
የአራተኛ ሩብ አመት በጀት አመቱን ስራዎች ማጠናቀቂያ ነዉ በተባለዉ መድረክ አመራር ላይ ያሉ አካላት የተሰጣቸው ሀላፊነት በአግባቡ በመፈፀም የህዝቡን ጥያቄዎች መመለስ የሚችል አመራር መስጠት ይገባቸዋል ተብሏል።
ሚያዚያ 15 ቀን 2017 ዓ.ም
