የአፍሪካን የአየር ትራንስፖርት ተደራሽነት ማስፋት ላይ ያተኮረ የኢትዮጵያ አቪዬሽን ፎረም በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል፡፡
በመድረኩ የኢትዮጵያና የአፍሪካን የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት ከዓለም ጋር ማስተሳሰር በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ምክክር እንደሚደረግ ተጠቁሟል፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአህጉር አቀፍ ደረጃ ትልቅ አስተዋፅኦ እያበረከተ እንደሚገኝ በመድረኩ ተጠቅሷል።
ፎረሙ በአፍሪካ አየር ትራንስፖርት ዘርፍ የሚስተዋሉ ችግሮችን መፍታት በሚቻልባቸው ሁኔታቸው ላይ እንደሚያተኩርም ተመላክቷል፡፡
ሚያዚያ 16 ቀን 2017 ዓ.ም
