የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ሩሲያ ከዩክሬን ጋር ስምምነት ላይ ለመድረስ ዝግጁ መሆኑዋን ገለጹ፡፡
የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ ሰርጌ ላቭሮቭ ሩሲያ የተጠናከረ ጥቃት ከከፈተች በኃላ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ፑቲን ጥቃቱን እንዲያቆሙ መጠየቃቸውን ተከትሎ ሀገራቸው ለስምምነት ዝግጁ ነች ያሉት፡፡
ሰርጌ ላቭሮቭ እንዳሉት ከዩክሬን ጋር ለመስማማት ዝግጁ ነን ሆኖም ግን አሁንም በተወሰኑ ነጥቦች ላይ መነጋገርና መግባባት ይኖርብናል ብለዋል፡፡
የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ለመድረስ ያለው ሂደት በትክክለኛ አቅጣጫ ላይ እንደሚገኝና ድርድሩም በአሜሪካ በኩል ይቀጥላል ብለዋል፡፡
የ ትራምፕ ልዩ መልእክተኛ ስቲቭ ዊትኮቭ በቅርቡ ሌላ ዙር የተኩስ አቁም ስምምነት ንግግር እንደሚጀመር እጠብቃለው ብለዋል ሲል ዴሊ ኒውስ ዘግቧል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ የትራምፕ ልዩ መልዕክተኛ ስቲቭ ዊትኮፍ ዛሬ ከፑቲን ጋር ይገናኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ትራምፕ “ስቲቭ ለሰላም የማያባራ ድምፅ ይሆናል፣ እናም ሁላችንንም እንድንኮራ ያደርገናል” ሲሉ ጽፈዋል።
ይህ ውይይት የሚካሄደው የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዩክሬንን እና ሩሲያን ከተቹ በኋላ ነው ።
ረቡዕ ዕለት ትራምፕ ባሰፈሩት መልዕክት ዘለንስኪ ክራይሚያን እንደ ሩሲያ ግዛት እውቅና ለመስጠት ፈቃደኛ አለመሆናቸው ለሰላም ድርድሩ “በጣም ጎጂ ነው” ብለዋል ።
በትሩዝ ሶሻል ገጻቸው ላይ በለጠፉት ጽሁፍ የዘለንስኪ መግለጫ “የጦርነት ጊዜውን ከማራዘም በስተቀር ምንም አያደርግም፡፡ እኛ ወደ ስምምነት በጣም ቀርበናል “ብለዋል፡፡
ትላንት ትራምፕ ፊታቸውን ወደ ፑቲንንም አዞረዋል “ቭላዲሚር ፑቲን አቁም በሳምንት 5000 ወታደሮች እየሞቱ ነው የሰላም ስምምነቱን እንጨርሰው!”ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል ሲል ቢቢሲ ነው የዘገበው፡፡
ገነነ ብርሃኑ
ሚያዚያ 16 ቀን 2017 ዓ.ም
