እስራኤል ስልታዊ ጥቃት እያደረሰች ነዉ በሚል ሪፖርቶች እየወጡ መሆኑን ተከትሎ 11 የፍልስጤም እስረኞችን ፈታለች።

የተለቀቁት እስረኞች ከእስራኤል እስር ቤቶች ካህን ዩኒስ ወደሚገኘዉ የአዉሮፓ ሆስፒታል ተዘዋዉረዋል፡፡

የታሳሪዎች እና የቀድሞ እስረኞች ጉዳይ ኮሚሽን እና የፍልስጤም እስረኞች ማህበር በቅርቡ ባወጡት የጋራ መግለጫ፤ የቀድሞ እስረኞች የሰጡት ምስክርነት የእስራኤል ባለስልጣናት የፍልስጤም እስረኞችን ሰብአዊ መብታቸዉን በመግፈፍ እና የስነ ልቦና ጥቃት እንዲደርስባቸው በማድረግ ያደረሱትን ሰፊ በደል ያሳያል ብለዋል፡፡

እየተካሄደ ባለዉ ጦርነት ከ19 ወራት በኋላም፣ የእስር ሁኔታው አልተሻለም፤እንዲያውም እየተባባሰ መሄዱን ቀጥሏል ሲል ሪፖርቱ አፅንዖት ሰጥቷል፡፡

ጭካኔ የተሞላበት አያያዝ አሁንም በመቀጠሉ የታሳሪዎቹን እጣ ፈንታ ለመወሰን ጊዜ ወሳኝ ሚና ይጫወታል ሲል አስታዉቋል፡፡

ከእስር የሚለቀቁት ፍልስጤማውያን እስረኞች ብዙውን ጊዜ በከፋ ሁኔታ ውስጥ ሆነዉ ነዉ፡፡ አስከሬኖች ላይ እንኳን በእስራኤል እስር ቤት እና በካምፕ ባለስልጣናት የደረሱ ብዙ የማሰቃየት ምልክቶች ይታያሉ ብሏል ሪፖርቱ።

በጋዛ እስረኞች ላይ የአስገድዶ መድፈር እና የፆታዊ ጥቃቶችም ተስፋፍቷል ብሏል።

በጥቅምት 2023 ከጋዛ ሰርጥ ከጠፉት ቁጥራቸው ከማይታወቁ ፍልስጤማውያን በተጨማሪ ከ9ሺህ 5መቶ በላይ ፍልስጤማውያን በእስራኤል እስር ቤቶች ውስጥ ይገኛሉ።

እስከዳር ግርማ

ሚያዚያ 21 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *