በኢትዮጵያ ወደ 1 መቶ 10 ሺህ የሚጠጉ ህብረት ስራ ማህበራት ቢኖሩም እንደ ቁጥራቸዉ መጠን ዉጤታማ አለመሆናቸዉን የኢትዮጵያ ህብረት ስራ ኮሚሽን ገልጿል፡፡
በኮምሽኑ የጽፈት ቤት ሃላፊ የሆኑት አቶ አንባዬ ወልዴ ከኢትዮ ኤፍ ኤም ጋር በነበራቸዉ ቆይታ፤ የህብረት ስራ ማህበራቱ ረጅም እድሜ ያላስቆጠሩና በሚጠበቅባቸዉ ልክም ዉጤታማ አይደሉም ብለዋል ፡፡
ሕብረት ስራ ማሕበራት የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችላቸው ለውጥ በትግበራ ላይ መሆኑን የጠቀሱት ሃላፊው፣ ሪፎርሙ የማኅበራቱን የአሠራር ሥርዓት የሚያዘምን፣ እንዲሁም ጠንካራ አደረጃጀት በመፍጠር የቁጥጥርና የክትትል ሥራን ለማጠናከር የሚያስችል እንደሆነ ተናግረዋል።
የማኅበራትን ኃብትና ንብረት ከብክነት በመጠበቅ፤ የአባላቱንና የኅብረተሰቡን ተጠቃሚነትን ለማሳደግ ኮሚሽኑ ከግንዛቤ ፈጠራ ጀምሮ የፋይናንስ ድጋፍ እንዲሁም ሌሎች የቁጥጥር ስራዎችን እንደሚሰራም አቶ አምባዬ አብራርተዋል ፡፡
ልዑል ወልዴ
ሚያዚያ 30 ቀን 2017 ዓ.ም
