የእዉቁ ካርዲዮሎጂስት ፍቅሩ ማሩ ስርአተ ቀብር በዛሬዉ ዕለት በስዊድን ሀገር ተፈፅሞ።

በኢትዮጵያ በልብ ህክምና ዘርፍ የመጀመሪያ የሆነዉን የልብ ህክምና ሆስፒታል ያቋቋሙት ካርዲዮሎጂስት ፍቅሩ ማሩ ባለፈዉ ዕሁድ ከዚህ አለም ድካም ማረፈቸዉንና በዛሬዉ ዕለት ቀብራቸዉ በስዊድን ሀገር ተፈፅሞል።

በሰለጠነዉ አለም ተምረዉ ወደ ትዉልድ ሀገራቸዉ በመምጣት በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነዉን የልብ ሆስፒታል በማቋቋም በልብ ህክምናዉ ከሩብ ክፍለ ዘመን በላይ ህዝባቸዉንና ሃገራቸዉ ያገለገለ ነበሩ።

የጥቁር አንበሳው የልብ ህሙማን ህክምና ማዕከል ፣ የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል፣ ጎንደር ዩኒቨርስቲና ሌሎቹም የልብ ህክምናን እንዲጀምሩ ካገዙት ውስጥ መሆናቸውን ነግረውናል፡፡

በትውልድ ኢትዮጵያዊ በዜግነት ሲዊድናዊ የሆኑት ዶ/ር ፍቅሩ ማሩ ካለፈው አንድ አመት ወዲህ የጤናቸው ነገር ታውኮ በህክምና ላይ እንደነበሩ የነገሩን ዶ/ር ቴዎድሮስ ከህልፊታቸው ከሳምንት በፊትም በአዲስ አበባ ተገኝተው የአዲስ የልብ ህክምና የማስፋፊያ ስራን መርቀው መመለሳቸውን ተናግረዋል፡፡

ሊዲያ ደሳለኝ

ግንቦት 1 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *