ከ 10 በላይ አፍሪካ ሃገራት የተሳተፉበት አለም አቀፍ የመላው አፍሪካ  የቆዳ ንግድ ትርኢት በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ

በ14ኛው አለም አቀፍ የመላው አፍሪካ  የቆዳ ንግድ ትርኢት ላይ  ከቆዳ አና ከቆዳ ጋር ተያያዥነት ያላቸው  ኢንድስትሪዎች ምርቶቻቸውን አቅርበዋል

በንግድ ትርኢቱ ላይ ከ 10 በላይ ከሆኑ የአፍሪካ ሃገራት የተውጣጡ 64 ኢንድስትሪዎች  ተገኝተዋል

አለም ላይ ካለው የእንሰሳት ሃብት 25 ፐርሰንት የሚሆነው   በአፍሪካ ነው የሚገኘው ያሉት የኢንድስትሪ ሚኒስተር ዴታው አቶ  ታረቀኝ ቡልልታ  ካለው ሃብት  እንፃር አፍሪካ መጠቀም አልቻለችም ብለዋል

እንደዚህ አይነት ኢግዚቢሺኖች የአፍሪካ ሃገራት በዘርፉ ያላቸውን አውቀት እና  የገበያ ተስስር  ለማጠናከር አይነተኛ ሚና ይወጣል ብለዋል

እንደ ሃገር  የቆዳ ምርት እስትራቴጂ በማዘጋጀት በዘርፉ ላይ ተግዳሮት የሆኑ ችግችን በመለየት አየተሰራ መሆኑን ሚኒስተር ዴታው  አስታውቀዋል::

አቤል እስጢፋኖስ

ግንቦት 15 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *