የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና የአካባቢና ማህበራዊ ተፅዕኖ ግምገማ አዋጅ መሻሻሉንም ገልጿል።
የህግ ክፍተቶች በነበሩባቸዉ ቦታዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች እንዲሁም ብክለትን የመቀነስ ስራዎች መስራቱንም ባለስልጣኑ አስታውቋል።
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የዓለም የአካባቢ ቀንን ለማክበር መዘጋጀቱንም ገልጿል። ዕለቱ በአለም ደረጃ ለ 52ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ 32ኛ ጊዜ የሚከበር መሆኑን የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር ሌሊሴ ነሜ ገልጸዋል።
ዋና ዳይሬክተሯ እንደገለፁት፤የፕላስቲክ ብክለትን፣ የአየር፣ የዉሃ፣ የአፈር እና የድምፅ ብክለትን እንዲሁም በአካባቢና በማህበራዊ ጉዳዮች ላይ የሚኖረውን ተፅዕኖ ግምገማ ተደርጓል።
በዚህም የነበሩ የህግ ክፍተቶችን በማየት ከ18 ዓመት በላይ የቆዩ ህጎች መሻሻላቸውን አስታውቀዋል።
ሀሙስ ግንቦት 28 “ፅዱ አትዮጵያ” በሚል መሪ ቃል የዓለም የአከባቢ ቀን ይከበራል።
ሊዲያ ደሳለኝ
ግንቦት 27 ቀን 2017 ዓ.ም
