ሩሲያ በዩክሬን መዲና ኪቭ እንዲሁም በኦዴሳ በሚገኝ ሆስፒታል ላይ ከፍተኛ የተባለ የድሮን ጥቃት አድርሳለች፡፡
በጥቃቱ ሁለት ሰዎች ህይወታቸዉ ሲያልፍ 12 ሰዎች ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል ሲሉ የከተማዉ ከንቲባ አስታዉቀዋል፡፡
በኦዴሳ የደረሰዉ ጥቃት የህክምና ማዕከላትን እና መኖሪያ ስፍራዎችን ኢላማ ያደረገ መሆኑ ተገልጿል፡፡
የድሮን ጥቃቱ ሩሲያ ዩክሬን ላይ ሰኞ ዕለት ካደረሰችዉ ጥቃት በኋላ በድጋሚ የደረሰ ሲሆን፤ ዩክሬን ከሰሞኑ በሩሲያ ላይ ላደረሰችዉ ጥቃት የመልስ ምት መሆኑንም ክሬምሊን አስታዉቋል፡፡
የኪቭ ወታደራዊ አስተዳደር ሃላፊ በተለያዩ ቦታዎች ላይ የደረሱት ጥቃቶች በድንገት የተከሰቱ መሆናቸዉን ገልጸዋል፡፡
በጥቃቱ ጉዳት የደረሰባቸዉ ዜጎች የህክምና ድጋፍ እያገኙ መሆናቸዉንም አስታዉቀዋል፡፡
የታመሙ እና በከባድ የቆሰሉ የጦር እስረኞች፣ ከ25 አመት በታች ያሉ እንዲሁም የ12ሺህ ወታደሮች አስከሬን መለዋወጥ መጀመሩን ተከትሎ ጥቃቱ መድረሱ ተዘግቧል፡፡
የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በፈረንጆቹ 2022 ዩክሬንን ሙሉ በሙሉ መዉረራቸዉ ይታወሳል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
እስከዳር ግርማ
ሰኔ 3 ቀን 2017 ዓ.ም
