ነዋሪነቷን በሰሜን አሜሪካ ያደረገችዉ ጋዜጠኛ ህይወት ታደሰ የኢትዮጵያ የልብ ህክምና ማዕከልን ለ5 አመታት ያህል ገቢ በማሰባሰብ ስትረዳ የነበረ ሲሆን፤ በዛሬዉ ዕለት ለልብ ማዕከሉ ይህን ማሽን አስረክባለች።
የበጎ አድራጎት ስራን ለማጠናከር በአሜሪካ ላይፍ ፎር አፍሪካ የተሰኘ ግብረ ሰናይ ድርጆት ማቋቋሟም ተገልጿል፡፡
ከተመሠረተ 30 አመታት የሆነዉ የኢትዮጵያ የልብ ህሙማን ማዕከል እስካሁን ከ 3ሺህ በላይ ህፃናትን ያለምንም ክፍያ ከሀገር ዉስጥና ከዉጭ በሚገኘዉ እርዳታ እንዲታከሙ አድርጓል።
በማዕከሉ በአሁን ሰአት ከሀገሪቱ አካባቢዎች የመጡ ከ 7ሺ በላይ ህፃናት የቀዶ ህክምና ለማግኘት በመጠባበቅ ላይ ናቸዉ።
ማህበራዊ ሚዲያን ለበጎ አላማ በመጠቀም ይህንን የህክምና መሣሪያ ለማዕከሉ ያስረከበችዉ ጋዜጠኛ ህይወት ታደሰን እና በመላዉ ዓለም የሚገኙ ለጋስ ኢትዮጵያዉያንን ማዕከሉ አመስግኗል።
6710 ላይ ok በማለት በቀን አንድ ብር ለኢትዮጵያ የልብ ህሙማን ህፃናት መርጃ ማዕከል ልገሳ እንዲደረግም ተቋሙ ጠይቋል፡፡
ሊዲያ ደሳለኝ
ሰኔ 5 ቀን 2017 ዓ.ም
