ኤቢሲ ኒውስ እንደዘገበው ወደ 4 ሺህ 800 የሚጠጉ የብሔራዊ ጥበቃ እና የዩኤስ የባህር ኃይል ወታደሮች በአሁኑ ጊዜ በሎስ አንጀለስ ይገኛሉ፡፡
ይህ ቁጥር በቅደም ተከተል በኢራቅ እና ሶሪያ ከተሠማሩት 2 ሺህ 500 እና 1 ሺህ 500 ወታደሮች ይበልጣል።
ሕገ-ወጥ ስደተኞች መታሠራቸውን ተከትሎ ተቃውሞዎች እየተባባሱ በመምጣታቸው ከምሽቱ 2 ሰዓት እስከ ንጋት 12 ሰዓት የሚቆይ የሰዓት እላፊ ገደብ ተጥሏል፡፡
ገደቡን የጣሱ የእስር ቅጣት እንደሚጠብቃቸው ተገልጿል።
ሰኔ 4 ቀን 2017 ዓ.ም
