የእስራኤል አየር ኃይል ማምሻውን በኢራን ኢላማዎች ላይ አምስት ዙር ጥቃት አካሂዷል ሲል ታይምስ ኦፍ እስራኤል ዘግቧል።
የኢራን መንፈሳዊ መሪ ለእስራኤል ጥቃቱ በተመለከተ በሰጡት ምላሽ”እስራኤል የመኖሪያ አካባቢዎችን በመምታት ከመቼውም ጊዜ በላይ የክፋት ባሕሪዋን አሳይታለች።” ብለዋል።
አያቶላ ከሊ ካሜኔ “ጠላት ከባድ ቅጣት” እንዲጠብቅ አስጠንቅቀዋል።
የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ እንዳሉት ወታደራዊ ዘመቻው አስፈላጊ እስከሆነ ድረስ ይቀጥላል ሲሉ ተደምጠዋል።
ኢራን በጥቃቱ ላይ የአሜሪካ እጅ አለበት ብትልም አሜሪካ ግን ክሱን ውድቅ አድርጋለች።
ሰኔ 6 ቀን 2017 ዓ.ም
