ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በዛሬው ዕለት የኬኛ ቤቨሬጅስ ኩባንያን መርቀው ሥራ አስጀምረዋል፡፡

በምርቃት ሥነ ሥርዓቱ ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ የፌደራልና የክልል ከፍተኛ አመራሮች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

ፕሬዚዳንት ታዬ ከ22 ቢሊየን ብር በላይ ኢንቨስት ተደርጎ በ110 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈውን የኬኛ ቤቬሬጅስ ኩባንያ ግንባታ ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡

በዓመት ከ3 ሚሊየን ሄክቶ ሊትር በላይ ማምረት የሚችለው ኩባንያው፤ በቴክኖሎጂ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ መሆን እንደሚችል ተገልጿል።

በአክሲዮን ማህበር የተመሰረተው ኩባንያው ከ4 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ባለ አክሲዮኖች፣ የህብረት ሥራ ማህበራትና ድርጅቶች በአንድ በመጣመር የሀገርን አቅም ያሳየ ሀገር በቀል ኩባንያ መሆኑም ተሰምቷል ፡፡

በአሁኑ ወቅት ለ250 ሰዎች የሥራ ዕድል የፈጠረ ሲሆን፤ በሙሉ አቅሙ ሥራ ሲጀምር ለ1 ሺህ ሰዎች የሥራ ዕድል እንደሚፈጥርም ተጠቁሟል፡፡

ሰኔ 7 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *