በባህልና ስፖርት ሚኒስቴር አዘጋጅነት በኦሮሚያ ክልል ጅማ ከተማ የሚካሄደው የ6ኛ መላው ኢትዮጵያ ጨዋታ የመክፈቻ መርሀ ግብር ተካሄደ።ዛሬ የተጀመረው 6ኛው የመላ ኢትዮጵያ ጨዋታ እሰከ ሰኔ 19/2017 ዓ.ም ድረስ የሚቀጥል ይሆናል።
የእለቱ የክብር እንግዶች ክብሩ አቶ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ፣ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ሸዊት ሻንካ፣ የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንት አቦሉ አብድ እንዲሁም የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ ባለስልጣን በመርሀ ግብሩ ታድመዋል።
“ስፖርት ለኅብር ኢትዮጵያ አርበኝነት” በሚል መሪ መልዕክት በሚካሄደው 6ኛው የመላ ኢትዮጵያ ጨዋታ ከክልሎች እና ከተማ አሥተዳደሮች የተውጣጡ ከ5000 በላይ የስፖርቱ ልዑካን ተሳታፊ ናቸው። ተወዳዳሪዎቹ በ26 የስፖርት ዓይነቶች ፉክክር እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።
ጋዲሳ መገርሳ
ሰኔ 10 ቀን 2017 ዓ.ም
