በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት 10 ወራት ከ 28 ሺ በላይ የንግድ ተቋማት አስተዳደራዊ እርምጃ ተወስዶባቸዋል ተባለ፡፡

እርምጃው የተወሰደው በተደረገ ክትትል ህገወጥ ስራ ሲሰሩ በመገኘታቸው እንደሆነ የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ አስታወቋል፡፡

የቢሮው ኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አሸናፊ ብርሀኑ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደገለፁት እርምጃ ከተወሰደባቸው ተቋማት መካከል ያለንግድ ፈቃድ ሲሰሩ የተገኙ ፤ያለ ዘርፍ የተሰማሩ ፤ ያለ አድራሻ እና ዋጋ ሳይለጥፉ ሲነግዱ የተገኙ ናቸው፡፡

ከዚህ ውስጥም ወደ 28 ሺ 3 መቶ14 የሚሆኑት ጥፋታቸውን እንዲያስተካክሉ ተደርጎ ወደ ስራ እንዲመለሱ መደረጉን ገልፀዋል፡፡

የተቀሩት 5 መቶ 57 የሚሆኑት ግን ጥፋታቸው ከፍተኛ በመሆኑ ከንግድ ስርአቱ እንዲወጡ ፣ንግድ ፈቃዳቸው እንዲሰረዝ እና በህግ እንዲጠየቁ መደረጉን ሃላፊው ገልፀዋል።

ህብረተሰቡም በከተማችን የንግድ ስርአት ላይ የሚያስተውላቸው ብልሹ አሰራሮች ካሉ 85-88 ላይ ጥቆማ በመስጠት ተባባሪ ይሁን ሲሉም አቶ አሸናፊ ብርሃኑ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ሐመረ ፍሬው

ሰኔ 11 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *