አስተያየት ሰጪዎች ለደህንነታቸዉ ሲባል እንዲሁም ተደጋጋሚ አስተያየቶች እንዳይሰጡ ማንነታቸዉን የሚደብቅ መሆኑም ተገልጿል፡፡
ለህዝብ አስተያየት ክፍት የሆኑ በፌደራልም ሆነ በክልል ቢሮዎች የሚወጡ ደንቦች፣ መመሪያዎች እንዲሁም አዋጆች ላይ ማህበረሰቡ ከመጽደቃቸዉ በፊት አስተያየት እንዲሰጥባቸዉ የሚያስችል መሆኑም ነዉ የተገለጸዉ፡፡
ከጣቢያችን ጋር ቆይታ ያደረጉት የሶፍትዌር ልማት ባለሙያ አቶ ዉበቱ ሽፈራዉ፤ ህጎች ከመጽደቃቸዉ በፊት ዜጎች ተሳትፎ እንዲኖራቸዉ ለማድረግ በማሰብ መዘጋጀቱን ይገልጻሉ፡፡
ዜጎች አስተያየት እንዲሰጡ የሚያስችለዉ ይህ ፖርታል፤ የተሰበሰበሰዉ አስተያየት ለሚቀጥለዉ ዙር ምክክር እንደ ግብዓት ሆኖ የሚያገለግል መሆኑን አንስተዋል፡፡
ህጎች ከመጽደቃቸዉ በፊት አስተያየት መሰብሰብ ከተፈለገ በዋነኝነት ዜጎች አስተያየት እንዲሰጡ ለማድረግ ዶክመንቶቹ ለግምገማ ይቀርባሉ ብለዋል አቶ ዉበቱ፡፡
በሚወጡት ህጎች ላይ የአስተያየት የሚሰጡ ዜጎች ለደህንነታቸዉ ሲባል እንዲሁም ተደጋጋሚ አስተያየቶች እንዳይሰጡ ማንነታቸዉ ግልጽ አይደረግም ብለዋል፡፡
ከዚህ በፊት ከህግ ባለሙያዎች፣ ግለሰቦች እንዲሁም የሲቪል ማህበራት ጋር በአካል ይደረጉ የነበሩ ምክክሮችን አሁን ላይ በኦንላይን ማድረግ የሚያስችል መሆኑንም ገልጸዋል፡፡
የፍትህ ሚኒስትር ድዔታዉ አቶ በላይሁን ይርጋ፤ አገልግሎቱ ማህበረሰቡ ጋር ተደራሽ እንዲሆን እና ተጠቃሚዎች የበለጠ እንዲረዱት የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራዎች እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡
‹‹ኢ-ኮንሰልቴሽን ፖርታል›› የተሰኘዉ ይህ አገልግሎት በአዉሮፓ ህብረት ድጋፍ በጂ-አይ-ዜድ በሚተገበረዉ የቤክ ፕሮጀክት በኢትዮጵያዊያን ባለሙያዎች የተዘጋጀ መሆኑን ሰምተናል፡፡
እስከዳር ግርማ
ሰኔ 12 ቀን 2017 ዓ.ም
