የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የጥላቻ ንግግር እና የሐሰተኛ መረጃ ስርጭትን የተመለከተ ሪፖርት በዛሬው እለት ይፋ አድርጓል።
ሪፖርቱ ያተኮረው ከ2016 ዓ.ም ጥር ወር ጀምሮ እስከ 2017 ዓ ም ጥር ወር ድረሰ ያለውን ነው ተብሏል ።
ሪፖርቱን ያቀረቡት የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የዋና ዳይሬክተሩ አማካሪ አቶ ታምራት ደጀኔ ፤በኢትዮጵያ በማህበራዊ ሚዲያ የሚለቀቁ የሃሰተኛ እና የጥላቻ ንግግር አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደረሷል ብለዋል።
አማካሪው እንደ ኢትዮ ቴሌኮም መረጃ መሰረት በኢትዮጵያ ከ44 ሚሊዮን በላይ የበይነ መረብ ተጠቃሚ አለ ብለዋል።
የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚው ለብቻው ወደ 4 ሚሊዮን ይጠጋሉ ያሉት አማካሪዉ፤በመቶኛ ሲሰላ 6 በመቶ ነው ብለዋል።ይህ ቁጥር በዋዛ የሚታይ አደለም ነው ያሉት።
ለሪፖርቱ ተአማኒነት እንዲያገለግል 1 ሺህ 700 የማህበረሰብ አስተያየት መጠየቃቸውን የተናገሩት አማካሪው አቶ ታምራት፤ከ5ሺህ በላይ ተከታይ ባላቸዉ ተጽኖ ፈጣሪዎች የሚለቀቁ የጥላቻና ሀሰተኛ መረጃዎች ከ2ሺህ በላይ ይዘቶች በባለሙያ ተለይቷል ብለዋል፡፡
እነዚህ የጥላቻ ንግግሮች በሰፊው የሚዘዋወሩት በፅሁፍና በምስል በታገዘ ቪዲዮ ሲሆን የሚዘዋወሩትም በፌሲቡክ፣ በቴሌግራምና በቲክቶክ ላይ ነው ብለዋል ።
56 በመቶ የሚሆነው የጥላቻ ንግግሮች የሚሰራጨው ተፅኖ ፈጣሪ በሆኑ ግለሰቦች እንደሆነም ተገልጿል።
እንደ ጥናት ሪፖርቱ ግኝት ከሆነ ከተለዩት 2 ሺህ ይዘቶች ዉስጥ ወደ 77 በመቶ የሚሆነው የፖለቲካ ይዘት ያለው ነዉ ብለዋል፡፡ቀሪዎቹ ብሔር 15 በመቶ፤ሃይማኖት 6 በመቶ መሆናቸዉንም ሰምተናል፡፡
እነዚህን የጥላቻ መረጃ የሚያዘዋውሩ ግለሰቦችን ለመቆጣጠር የሚያስችል ህግና ስርዓት ያለመኖሩ ችግር መፍጠሩንም ገልፀው፤ይህን መቆጣጠር የሚያስች ደንብ መውጣት አለበት ብለዋል።
ሆኖም ጎልቶ የወጡትን ችግሮች መፍትሄ ለመስጠት መሰራት አለባቸዉ ብለዉ አማካሪዉ ካስቀመተዋቻ ነጥቦች መካከል፤አንደኛዉ የማህበራዊ አገልግሎት ሰጪ ኩባኒያዎች የአቅም ግንባታ ስራዎች እንዲሰሩ መደረግ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
ሌላዉ እንደ ሜታ ያሉ ማህበራዊ አገልግሎት የሚሰጡ ኩባኒያዎች በሌሎች የአፍሪካ ሃገሮች ላይ እንደ ከፈቱት ቅርንጫፍ ጽፈት ቤት በርካታ ተጠቃሚዎች ባሉባቸዉ ኢትዮጵያም እንዲከፍቱ መደረግ አለበትም ተብሏል፡፡
ሶስተኛዉ ኩባኒያዎቹ የሚሰጡት አገልግሎቶች የኢትዮጵያን ብሄራዊ ጥቅም ባስጠበቀ መልኩ አሰራራቸዉን እንዲያሻሽሉ ማድረግ ያስፈልጋልም ብለዋል፡፡
እንደ መንግስት በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጩ ሃሰተኛ እና የጥላቻ መረጃዎችን የሚመለከት የፖሊሲና የህግ ማእቀፍ ባለመኖሩ ተጠያቂነትን ለማስፈን እንዲያስችል ህግ ተብራርቶ በዝረዝር መዉጣት አለበት ተብሏል፡፡
የተቋሙ የዚህ ሪፖርት ዓላማም በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የጥላቻ ንግግር እና የሐሰተኛ መረጃ ስርጭት የሚገኝበትን ሁኔታ እና ከጊዜ ወደ ጊዜ የሚያሳየውን እድገትና አሉታዊ ተፅዕኖ በማመላከት የመፍትሄ ሀሳብ ለመጠቆም ያለመ ነው ብለዋል፡፡
የጥላቻ ንግግር እና ሐሰተኛ መረጃን ስርጭትን የመከላከል ስራ ለተወሰኑ ተቋማት ብቻ የተሰጠ ሃላፊነት ሳይሆን የሁሉንም ተቋማትና ግለሰቦች ትብብር የሚጠይቅ ስለሆነ የጥላቻ ንግግርና ሐሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመግታት በሚደረገው ሂደት ሁሉም ሃላፊነቱን ሊወጣ እንዲሚገባ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ልኡል ወልዴ
ሰኔ 12 ቀን 2017 ዓ.
