እስራኤል ካትስ የኢራን የበላይ መሪ ከእንግዲህ እንዲኖሩ ሊፈቀድላቸው አይገባም አሉ፡፡

በደቡባዊ እስራኤል የሚገኘው የሶሮካ ሆስፒታል በኢራን የሚሳኤል ጥቃት ከተመታ በኋላ የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

የኢራን ጠቅላይ መሪ አያቶላ አሊ ካሜኔይ ከእንግዲህ መኖር አይገባቸዉም ሲሉ የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር መናገራቸዉን አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘግቧል።

ጠቅላይ መሪዉ፤ እስራኤል እንድትጠፋ እንደሚፈልጉ በግልፅ ተናግረዋል፡፡

በግላቸውም በሆስፒታሎች ላይ ጥቃት እንዲፈጸም ትዕዛዝ ሰጥተዋል፤ የእስራኤልን መንግሥት መጥፋትም እንደ ግብ ይቆጥሩታል ብለዋል፡፡

እንዲህ ያለው ሰው ከአሁን በኋላ እንዲኖር ሊፈቀድለት አይገባም ሲሉም ለጋዜጠኞች ተናግረዋል ሲል ዘ ጋርዲያን ዘግቧል፡፡

እስከዳር ግርማ

ሰኔ 12 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *