ባንኩ ሰኔ 12 ቀን 2017 ዓ.ም በሒልተን ሆቴል የመንግስት ሀላፊዎችና የቀድሞ ባለስልጣናት በተገኙበት ይፋ እንዳደረገው፣
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከዓለም ባንክ የሥርዓተ-ፆታ ፈጠራ ጋር በመተባበር ባካሄዱት የ2025 የባንኮች የስርዓተ ፆታ አካታችነት ምዘና መስፈርት ከ30 የኢትዮጵያ ባንኮች የመጀመሪያና ብቸኛ ባንክ ሆኗል።
በባንኩ ከ55 በመቶ በላይ አመራሮች ሴቶች መሆናቸው፣ ከ22 ሺ በላይ ለሆኑ ስራ ፈጣሪ ሴቶች 1.4 ቢሊየን ብር ካለ ዋስትና በማበደር የራሳቸውን ስራ እንዲጀምሩ መደረጉ፣ እንዲሁም ሴቶች ላይ ብቻ ትኩረቱን አድርጎ የሚሰራ ክፍል በማዋቀር ሴቶችን በቢዝነስና መሰል ስራዎች የማማከር ስራ እየሰራ መሆኑ ባንኩ ከተመረጠባቸው መስፈርቶች መካከል እንደሆነ ገልጿል።
እናት ባንክ በተመረጠበት ዘርፍ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፓኪስታን በመቀጠል ሁለተኛዋ ሀገር ሆና ተቀምጣለች በማለትም አስታውቋል።
አዲስዓለም አበበ
ሰኔ 13 ቀን 2017 ዓ.ም
