በዩክሬን መዲና ኪቭ በደረሰ ከባድ የዓየር ጥቃት ቢያንስ 10 ሰዎች ህይወታቸዉ አልፏል ተባለ፡፡

በዩክሬን መዲና እና አከባቢዉ ላይ ሩሲያ ባደረሰችዉ ከባድ የድሮን እና የሚሳዔል ጥቃት ቢያንስ 10 ሰዎች ተገድለዋል ሲሉ የአከባቢዉ ባለስልጣናት ተናግረዋል፡፡

በዋና ከተማዋ የሚገኙ የተለያዩ ስፍራዎች ላይ የሚገኙ መኖሪያ ቤቶች የጥቃቱ ኢላማ መደረጋቸዉም ነዉ የተገለጸዉ፡፡

የደረሰዉ ጥቃት በአንድ ሳምንት ውስጥ የተከሰተ ሁለተኛዉ ትልቅ ጥቃት መሆኑም ተገልጿል፡፡

እስራኤል በኢራን ላይ የከፈተችዉን የአየር ዘመቻ ለመቀላቀል አሜሪካ ዉሳኔ ማሳለፏን ተከትሎ የአለም ትኩረት ወደ ሌላ አቅጣጫ በመዞሩ የተፈጠረዉን ግፊት ከፍ ለማድረግ ፍላጎት እንዳላት የሚያሳይ ነዉ ተብሏል፡፡

ሩሲያ 3መቶ52 ድሮን፣ 11 ባለስቲክ ሚሳዔል እንዲሁም 5 ክሩዝ ሚሳዔሎችን በአንድ ሌሊት መተኮሷን የዩክሬን አየር ኃይል አስታዉቋል፡፡

የአየር መከላከያዎች አብዛኞቹን ጥቃቶች ኢላማቸው ላይ ከመድረሳቸዉ በፊት በመጥለፍ ማጨናገፉንም ገልጿል።

እስከዳር ግርማ

ሰኔ 16 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *