የኢትዮጵያ እድገት ከውጭ እንደሚባለው “የኮሪደር ልማት ሳይሆን ብዝሀ ዘርፍን ያማከለ ነው” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ
ይህ የተገለጸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ላነሷቸው ጥያቄዎች ምላሽ በሰጡበት ወቅት ነው
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ “ትኩረቱ ኮሪደር ብቻ ሆነ ብላችሁ ያነሳችሁት ከዚህ ቀደም በነበሩት መን ግስታት አንዲሁም አመረራ የትኩረት ማነስ ስለሆነ ብቻ ነው ያሉ ሲሆን ፤መንግሰት ግን በተለያዩ መስኮቸች ላይ እየሰራ ነው” ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ አሁን የያዘችውን እድገት ለማሳካት ኢትዮጵያ ብዙ ፈተናዎችን አይታለች ያሉ ሲሆን፤ በተለይም አለም አቀፍ የንግድ አንዲሁም መሰል ስርዓቱ ባለበት ችግር ምከንያት ተፈትና ቆይታለች ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ ጥቅል ኢኮኖሚውን ለማሳደግ ብዙ ሰርታለች ያሉ ሲሆን ኢኮኖሚው “ከውጭ እንደሚባለው ኮሪደር ልማቱ ላይ ብቻ ትኩረት ያደረገ ሳይሆን ብዙሃኑን ዘርፍ ያማከለ ነው” ብለዋል፡፡
በግበርናው ዘርፍ ትራክተር የግብርና ኤክስቴሽን ባለሞያዎቸ እንዲሁም የተለያዩ መሳሪያዎቸን በመስጠት ሃብት ሰብስብን እየሰራን ትኩረት ለኮሪደር ብቻ ነው ማለት አይገባም ብለዋል፡፡
በዘንድሮው አመት 36.8 ሚሊየን ሄክታር መሬት ማረስ መቻሉንም ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ያነሱ ሲሆን ከምርት አኳያ ከአምናው በተሻለ መልኩ በ24.7በመቶ እድገት አሳክታለችም ብለዋል፡፡
በዚህም በግብርናው ዘርፍ 6.1 በመቶ እድገት አሳክታለች ሲሉም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለምክር ቤት ለአባላቱ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
ለዓለም አሰፋ
ሰኔ 26 ቀን 2017 ዓ.ም
