በአዲስ አበባ 7 ሺህ 277 የሚሆኑ ዛፎች ለኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ተጠግተው ተገኝተዋል ተባለ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በሀገር አቀፍ ደረጃ 55 ሺህ 325 ዛፎች ከኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት ጋር ንኪኪ እንዳለቸዉ ማረጋገጥ ችያለሁ ብሏል።

ተቋሙ ዛሬ በሰጠዉ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንዳስታወቀዉ በአዲስ አበባ ያሉ 152 የመካከለኛ መሥመሮች እና እነዚህን መሥመሮች የሚሸከሙ 59 ሺህ 48 ምሰሶዎች ላይ ጥልቅ ፍተሻ ማድረጉን ገልፆል።

ይህንን የገለፁት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የኔትወርክ መሠረተ ልማት ኦፕሬሽን ኤክሰለንስ ዳይሬክተር አቶ ፈሪድ አብዱልሰላም ናቸዉ።

ዳይሬክተሩ በአዲስ አበባ ከተማ የኤሌክትሪክ ፍሰቱ ከሀይል ማመንጫ ወደ ደንበኛዉ የሚያደርገዉን ፍሰት ላይ ያሉ ችግሮችን በፍተሻዉ መለየታቸዉን አንስተዋል።

ተደርጓል በተባለዉ ፍተሻ ከ25 ሺህ 973 ከባድና ቀላል የኃይል መቋረጥ መንስኤ የሆኑ ግኝቶች እንደተለዩ ሰምተናል።

የዛፎች ንክኪ 47 በመቶ ከሀይል መቆራረጥ መንስኤነት ጠቅሷል።

በዚህም አዲስ አበባ ላይ 7 ሺህ 277 የሚሆኑ ዛፎች ወደ መሰረተ ልማቱ ተጠግተው የተገኙ ሲሆን ተቋሙ 5 ሺህ 585 የሚሆኑትን ማፅዳት ተችሏል ብሏል።

ዳይሬክተሩ መቀየር የሚያስፈልጋቸው ምሰሶዎች፣ ከግንባታዎችና እርስ በእርሳቸው የተቀራረቡ መሥመሮች፣ የረገቡ እና የተለያዩ የመስመር ችግር ያለባቸው መገኘቱን ጠቅሰዋል።

በዚህም በአዲስ አበባ ላይ ከተገኙ ግኝቶች መካከል እስካሁን 56 በመቶ ወይም ለ14 ሺህ 649 ያህሉ አስፈላጊው ማስተካከያ ተደርጓል ተብሏል።

በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር 100 ሺህ ችግኞችን ለመትከል ዝግጅቱን እንዳጠናቀቀ አገልግሎት በሰጠዉ ጋዜጣዊ መግለጫ ተናግሯል።

ቁምነገር አየለ

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *