በከተማዋ ከ2 መቶ በላይ የሚሆኑ  ትራንስፎርመሮችን  አቅም ማሳደግ ተችሏል ተባለ

በአዲስ አበባ በሚገኙ 10 ሺህ 498 ትራንስፎርመሮች ላይ ምርመራ መደረጉን ሰምተናል።

የኢትዩጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በከተማዋ ባሉ ትራንስፎርመሮች ላይ አደረጉት ባለዉ ምርመራ ትራንስፎርመሮቹ ላይ  መጠነኛ ችግሮች ማግኘቱን ገልፆል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የኔትወርክ መሠረተ ልማት ኦፕሬሽን ኤክሰለንስ ዳይሬክተር አቶ ፈሪድ አብዱልሰላም ከ 2 መቶ በላይ በሚሆኑ ትራንስፎርመሮች ላይ የአቅም ማሳደግ ስራ እንደተሰራ ተናግረዋል።

“የደንበኞች መጨመር እንዲሁም የደንበኞች የሀይል አጠቃቀም ከ ጊዜ ወደ ጊዜ መቀየር እና  እያደገ መምጣት የትራንስፎርመሮች  መጨናነቅ እየጨመረ እንዲመጣ አድርጓል” ሲሉ ዳይሬክተሩ ገልፀዋል።

በሀገር አቀፍ ደረጃ የሃይል መቆራረጡን ወደ ዜሮ ለማምጣት የ100 ቀን ዕቅድ ተለይቶ ሲሰራ መቆየቱን አገልግሎቱ አስታዉቋል።

አቶ ፈሪድ የትራንስፎርመር አቅም ጋር በተያያዘ ችግሮችን ለመቅረፍ በኘሮጀክት እየተሰራ መሆኑን አንስተዋል።

በአንድ አመት ዉስጥ ይጠናቀቃል ተብሎ በተያዘዉ ኘሮጀክት ዉስጥ የ2 ሺህ ትራንስፎርመር አቅም ማሳደግ በተጨማሪም 2 ሺህ አጋዥ የትራንስፎርመር ስራዎች እንደሚኖር ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል።

በሌላ በኩል ከአዲስ አበባ ዉጪ ባሉ  28 ሪጅኖች ላይ ከ250 ሺህ በላይ የሀይል መቆራረጥ የግኝት ነጥቦች መገኘታቸው ተነግሯል።

ቁምነገር አየለ

ሰኔ 30 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *