በግብርናው እና ኢኮኖሚ ዘርፍ ላይ የሚያተኩረዉ ፎረሙ በዓድዋ ድል መታሰቢያ እየተካሄደ ይገኛል።
በፎረሙ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የኢፌዴሪ ም/ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ፎረሙ ላለፉት ሁለት ተከታታይ ዓመታት እንደ አህጉር ያለውን እምቅ ሃብት ወደ ተጨባጭ አቅም ለመቀየር ዕድል በሚፈጥር መልኩ መካሄዱን ተናግረዋል።
የስራ እና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል
በበኩላቸው ይህ የስራ እድል ኮንፈረንስ ብዙ ተመርቀው ስራ እየጠበቁ ያሉ ወጣቶች ኔትወርክ በመፍጠር ስራ ፈጣሪ እንዲሆኑ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።
በተለይም በሚሊዮን የሚቆጠሩ ወጣት አፍሪካውያን በየዓመቱ ወደ ሥራ ገበያው እንደሚገቡ ሚኒስትሯን ገልጸዉ ዘላቂ የሥራ እድል እንዲፈጠርላቸው ለኢኮኖሚያዊ መረጋጋት እና ማህበራዊ ልማት ወሳኝ እንደሆነም አንስተዋል።
ፎረሙ ከዛሬ ሰኔ 30 ጀምሮ እስከ ሀምሌ 2 ቀን 2017 አም ድረስ የሚቆይ ይሆናል።
ለዓለም አሰፋ
ሰኔ 30 ቀን 2017 ዓ.ም
