በአማራ ክልል ከ 8 ሺህ በላይ ቤቶችን በበጎ ፍቃድ አገልግሎት ለማደስ እና ለመገንባት መታቀዱ ተገለፀ

በክልሉ ከ 8 ሺህ በላይ ቤቶችን በክረምቱ መርሃ ግብር በጎ ፍቃድ አገልግሎት ለማደስ እና ለመገንባት በማቀድ እንቅስቃሴ መጀመሩን ርዕሰ መስተዳደር አረጋ ከበደ ገልፀዋል፡፡

ህዝቡ ባልተደራጀ መልኩም ቢሆን የመረዳዳት ባህል ያለው ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ ያለውን አቅም በማደራጀት ወደ ስራ ማስገባት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳደሩ ይሄን ያሉት የክልሉን የዘንድሮ አመት የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት መርሃ ግብር ባስጀመሩበት ወቅት ነው፡፡

በአማራ ክልል በተጀመረው የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት የቤት እድሳት፤ የደም ልገሳ፤ ችግኝ ተከላ እንዲሁም ሌሎች ተግባራት እንደሚከናወኑ ርዕሰ መስተዳደር አረጋ ከበደ አስታውቀዋል፡፡

የክልሉ የዘንድሮ የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት በጎነት ለኢትዮጲያ ከፍታ በሚል መሪ ቃል በይፋ ተጀምሯል፡፡

አቤል እስጢፋኖስ

ሐምሌ 3 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *