ትራምፕ ብራዚል ላይ 50 በመቶ ታሪፍ እንደሚጥሉ በመዛት የአገሪቱ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ክስ እንዲቋረጥ ጠየቁ

የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከደቡብ አሜሪካዋ አገር ጋር የገቡበትን እሰጣ ገባ በሚያባብስ ሁኔታ በብራዚል በተመረቱ ሸቀጦች ላይ የ50 በመቶ ቀረጥ ለመጣል ማቀዳቸውን ገለጹ።

ትራምፕ ይህንን እቅዳቸውን ይፋ ያደረጉት በማኅበራዊ ሚዲያ በተሰራጨው በሰሞነኛው የታሪፍ ደብዳቤ ነው።

ፕሬዝዳንቱ በዚህ ደብዳቤ፤ ብራዚልን በአሜሪካ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ላይ “ጥቃት” በመሰንዘር እና በቀድሞው ቀኝ አክራሪ ፕሬዝዳንት ዣየር ቦልሶናሮ ላይ “የሀሰት ውንጀላ ምርመራ” በማካሄድ ከስሰዋል።

ቦልሶናሮ፤ በ2022 የተካሄደውን የአገሪቱ ምርጫ ውጤት በመገልበጥ ሴራ በነበራቸው በተባለው ሚና ምክንያት ክስ ላይ ናቸው።

የብራዚል ፕሬዚዳንት ሉዊዝ ኢናሲዮ ሉላ ዳ ሲልቫ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ በብራዚል ላይ የሚደረገው የግብር ጭማሪ የአጸፋ ምላሽ እንደሚያስከትል የገለጹ ሲሆን በአገሪቱ የፍትህ ስርዓት ላይም ማንኛውም ዓይነት ጣልቃ ገብነት እንዳይደረግ አስጠንቅቀዋል ቢቢሲ ዘግቧል።

ሐምሌ 3 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *