የዕድሜ ባለጸጋዉ ፕሬዝዳንት ምርጫ እንደሚወዳደሩ ገለፁ።

የ92 አመቱ የካሜሮን ፕሬዝዳንት ፖል ቢያ፤ ለሌላ የስልጣን ዘመን የመወዳደር ፍላጎት እንዳላቸው በማህበራዊ ሚዲያ ገጻቸው አስታውቀዋል።

‹‹የተሻለዉ ገና ይመጣል››ያሉት ፕሬዝዳንቱ ከአሁን በኋላም ሀገራቸውን ለማገልገል እንደሚፈለጉ ገልጸዋል።

ፕሬዝዳንቱ እንደገና ለመመረጥ ማሰባቸው ሀገሪቷ ውስጥ ባሉ ተቃዋሚ ፖለቲከኞች እና የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ተቃውሞ እንዲገጥማቸው አድርጓል።

የካሜሮን የፖለቲካ ሽግግር መቆሙን ያሳያል ያሉት ተቃዋሚዎቹ፤ አገሪቱ ወደሌላ የምርጫ ኡደት እየገሰገሰች ባለችበት በአሁኑ ጊዜ ለሌላ የስልጣን ዘመን ለመወዳደር ማሰባቸው በካሜሮን ውስብስብ የፖለቲካ ሁኔታ ውስጥ አወዛጋቢ ምዕራፍ ነው ሲሉ ገልፀዋል።

ፖል ቢያ ከ40 አመታት በላይ ካሜሮንን በመምራት የቆዩ ሲሆን፤ በአፍሪካ ሁለተኛው ረጅም ጊዜ ያስቆጠሩ መሪ ያደርጋቸዋል።

ሀሚድ አብደላ

ሐምሌ 7 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *