ከፑቲን ጋር በነበረኝ ንግግር ደስተኛ ባልሆንም አሁንም ያልጨረስኩት ጉዳይ አለኝ ብለዋል ትራምፕ፡፡

ዶናልድ ትራምፕ ለቢቢሲ በሰጡት ቃለ መጠይቅ፤ ከፑቲን ጋር የነበራቸዉ ልዩ የስልክ ለዉዉጥ ተስፋ ቢስ ቢሆንም ጉዳዩን ግን አልጨረስኩም ነዉ ያሉት፡፡

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት የሩሲያውን መሪ እንደሚያምኗቸዉ ተጠይቀው በሰጡት ምላሽም፤ ማንም ሰው አላምንም ማለት ይቻላል ብለዋል፡፡

ትራምፕ ይህን የተናገሩት ለዩክሬን የጦር መሳሪያ ለመላክ ማቀዳቸውን ካስታወቁ ከሰዓታት በኋላ ሲሆን፤ በ50 ቀናት ውስጥ የእርቅ ስምምነት ካልተደረሰ በሩሲያ ላይ ከባድ ታሪፎች እንደሚጣሉ አስጠንቅቀዋል።

ትራምፕ በዩክሬን ጦርነትን ለማቆም ከሩሲያ ጋር ስምምነት ላይ ለመድረስ ለአራት ጊዜ ያህል አስበው እንደነበር ተናግረዋል።

ስለ ፑቲን ተጠይቀዉ በሰጡት ምላሽም ‹‹በእርሱ ተስፋ ብቆርጥም አልጨረስኩም። በእርሱ ግን ተስፋ ቆርጫለሁ››ሲሉ መልሰዋል፡፡

‹‹ጥሩ ውይይት እናደርጋለን፤ሂደቱም ጥሩ ነው ብዬ ሊሳካ እንደምንቃረብ ሳስብ እሱ በኪቭ አንድ ሕንፃ ያፈርሳል›› ብለዋል።

ሩሲያ በቅርብ ሳምንታት በዩክሬን ከተሞች ላይ የምታደርገውን የድሮን እና የሚሳኤል ጥቃት በማጠናከር ከዚህ በፊት ታይቶ የማይታወቅ የንጹሃን ሞት እንዲከሰት ሆኗል፡፡

ፑቲን ሰላምን እንደሚፈልጉ አጥብቀው የገለጹ ሲሆን፤ የጦርነቱ ‹‹ዋና መንስኤዎች›› መጀመሪያ መፈታት አለባቸው ብለዋል ሲል የዘገበዉ ቢቢሲ ነዉ።

እስከዳር ግርማ

ሐምሌ 8 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *