የናይጄሪያ የዋጋ ግሽበት በሰኔ ወር ላይ መቀነሱን በመግለፅ ይህም ለተከታታይ ሶስተኛ ወር መሆኑን የሀገሪቱ ብሔራዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ አስታዉቋል፡፡
ግንቦት ወር ላይ ከነበረው የዋጋ ግሽበት 22.97 በመቶ በሰኔ ወር ወደ 22.22 በመቶ ቀንሷል ተብሏል።
በባለፈው ዓመት የዋጋ ግሽበቱ ከፍተኛ ደረጃ ላይ መደረሱ የተገለጸ ሲሆን፤ በዚህም ምክንያት በሀገሪቱ ያለው የኑሮ ውድነት ቀውስ እየተባባሰ መጥቷል ነዉ የተባለዉ።
ካለፉት ዓመታት ሲነጻጸር የዋጋ ንረቱ መቀዛቀዝ ቢያሳይም፤ የምግብ እና የሸቀጦች ዋጋ በብዙ ናይጄሪያውያን ገቢ ላይ ጫና እየፈጠረ ነው ።
በናይጄሪያ በሰኔ ወር ላይ በዋና ዋና ከተሞች ላይ በተደረገ ሰልፍ የኑሮ ውድነት የብዙ ዜጎች አንገብጋቢ ጉዳይ እንደሆነ ተገልጿል፡፡
በአገሪቱ ውስጥ ያለው የኢኮኖሚ ውጥረት ገና እንዳልተጠናቀቀ የሚያሳዩ ምልክቶች አልጠፉም ሲል ያስነበበዉ አፍሪካ ኒዉስ ነዉ።
ኤርሚያስ ገረመዉ
ሐምሌ 10 ቀን 2017 ዓ.ም
