በዋና ከተማዋ ዳካ ውስጥ የአየር ኃይሉ የስልጠና አውሮፕላን በኮሌጅ ግቢ ውስጥ በመከስከሱ ህይወታቸዉ ካለፈዉ ዉስጥ አብዛኛዎቹ ተማሪዎች ሲሆኑ፤ ከ50 በላይ የሚሆኑት ደግሞ ቆስለዋል።
አውሮፕላኑ በዳካ ኡታራ አካባቢ በሚገኘው ኮሌጅ ግቢ ላይ ተማሪዎች ፈተና በሚወስዱበት እና መደበኛ ክፍላቸውን በሚከታተሉበት ወቅት መከስከሱ ነዉ የተገለጸዉ፡፡
ህጻናትንና ጎልማሶችን ጨምሮ ከ50 በላይ ሰዎች ከአደጋዉ በኋላ በደረሰባቸው ቃጠሎ ሆስፒታል መግባታቸውን የህክምና ባለሙያዎች ተናግረዋል።
የጤና ባለሙያዎች ለሮይተርስ የዜና ወኪል እንደተናገሩት፤ አንድ የሶስተኛ ክፍል ተማሪ ህይወቱ አልፎ መድረሱን እና ሌሎች ሶስት፤እድሜያቸው 12፣ 14 እና 40 የሆኑ ግለሰቦች ወደ ሆስፒታል ገብተዋል ብለዋል።
ሊዲያ ደሳለኝ
ሀምሌ 14/2017 ዓ.ም
