በሴቶች የአውሮፓ ዋንጫ ግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ ስፔን ጀርመንን በማሸነፍ የዋንጫ ተፋላሚ ሆነች By ethiofmAdminJuly 24, 2025July 24, 2025ስፖርት ከ90 ደቂቃ በላይ ግብ ሳይቆጠርበት የተጓዘው የጀርመን እና ስፔን ጨዋታ በተጨማሪ ሰአት ላይ የአሸናፊነቱን ጎል ቦንማቲ አስቆጥራ ስፔንን አሸናፊ ማድረግ ችላለች ። የፊታችን እሁድ የአለም ሻምፒዮኖቹ ስፔኖች ለመጀመሪያ ጊዜ የ አውሮፓ ዋንጫን ለማሳካት ከ እንግሊዝ ብሔራዊ ብድን ጋር ከባድ የፍፃሜ ፍልሚያ ይጠብቃቸዋል ። ኤርሚያሰ ገረመዉ ሐምሌ 17/2017 ዓ.ም