ሩሲያ ከወታደራዊ ትብብር በተጨማሪ ንግዷን ለማሳደግ የሚያስችላትን በረራ ወደ ሰሜን ኮሪያ ጀመረች

ከ70 ዓመት የዲፕሎማሲ ግንኙነት ቡኋላ ሩሲያ የንግድ በረራ ወደ ሰሜን ኮሪያ መጀመሯን ገልፃለች።

የኖርድዋይንድ አየር መንገድ የመንገደኞች ተቆጣጣሪ ባለስልጣን ኦሌግ ፤ከሞስኮ ወደ ፒዮንግያንግ የሚደረገው ቀጥተኛ የንግድ በረራ “ታሪካዊ ክስተት ነው” ሲሉ ተናግረዋል።

ከዚህ ባለፈ ሀገራቱ ከሚያደርጉት ወታደራዊ ትብብር ባለፈ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን ለማሳደግና በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የንግድ ግንኙነትን ይበልጥ ለማጠናከር ያግዛል ብለዋል።

የሩሲያ የትራንስፖርት ሚኒስቴር በበኩሉ ወደ ዋና መዲናዎቹ የሚደረገው በረራ ስምንት ሰዓት እንደሚፈጅ ገልጿ፤ አገልግሎቱ በወር አንድ ጊዜ ይሰጣል ሲልም አስታውቋል ።

የሩሲያ ብሔራዊ መገናኛ ብዙሃን ታስ እንደ ዘገበው ከሆነ ደግሞ የመጀመሪያው የመልስ በረራ ከፒዮንግያንግ ወደ ሞስኮ ማክሰኞ ይደረጋል።

በተጨማሪም ሁለቱ ሀገራት በኮቪድ 19 ጊዜ በ2020 አቋርጠውት የነበረውን የባቡር ትራንፖርት አገልግሎት ማስጀመራቸውንም ገልፀዋል።

ሁለቱ ሀገራት በቅርብ ዓመታት ውስጥ የበለጠ ወታደራዊ ትስስር በመፍጠር ፒዮንግያንግ ሩሲያ በዩክሬን ለምታደርገው ወታደራዊ ዘመቻ ወታደሮችን እና የጦር መሳሪያዎችን አቅርባለች።

ባለፈው ዓመት የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ሰሜን ኮሪያን ሲጎበኙ የጋራ መከላከያ ላይ ያተኮረ ወታደራዊ ስምምነት መፈራረማቸው ይታወሳል ሲል የዘገባው ኢንሳይደር ፔፐር ነው።

ልዑል ወልዴ

ሐምሌ 21/2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *