እስራኤል በጋዛ በየቀኑ ለተወሰነ ሰዓት የሚቆይ የተኩስ አቁም አወጀች።

እስራኤል በጋዛ የእርዳታ አቅርቦት እንዲካሄድ ለማስቻል በየቀኑ ለ10 ሰዓት የሚቆይ የተኩስ አቁም ማወጇን አስታውቃለች።

የዓለም ምግብ ፕሮግራም ከሁለት ሚሊየን በላይ የጋዛ ነዋሪዎች መካከል አንድ ሶስተኛው ያለ ምግብ ቀናት እንዳሳለፉ ገልጿል ።

የተመጣጠነ ምግብ ዕጥረት ያለባቸው ህጻናት አሳዛኝ ምስሎች በመላው አለም ተሰራጭተዋል፡፡

ይህም በእስራኤል እና የቅርብ አጋሮች ላይ ቀጣይነት ባለው ጦርነት እና በቀሰቀሰው የሰብዓዊ ቀውስ ከፍተኛ ትችትን አስከትሏል።

ሐማስ ‹‹የራሱን ምስል እያጸዳ ነው›› ስትል የምትከሰዉ እስራኤል፤‹‹ሆን ብላ ታስርባለች የሚለውን ሐሰተኛ ውንጀላም አልቀበለውም›› ብላለች።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ቮልከር ተርክ፤ ከግንቦት ወር ጀምሮ ምግብ ለማግኘት ሲሞክሩ ከ1 ሺህ በላይ ሰዎች መገደላቸውን ጠቅሰው ሁኔታው ‹‹አስፈሪ›› ነው ሲሉ ገልጸዉታል፡፡

የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ፤ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ‹‹ምክንያት እና ውሸት›› እያቀረበ ነው ሲሉ በመወንጀል እስራኤል በፀጥታ መንገዶች የሰብዓዊ እርዳታ እንዲገባ እየፈቀደች ነው በማለት መልስ ሰጥተዋል።

ተቃውሞው እየጨመረ በመምጣቱ የእስራኤል ጦር የእርዳታ ስርጭት እና የሲቪሎች እንቅስቃሴ እንዲኖር ብዙ ህዝብ በሚኖርባቸው ሶስት አካባቢዎች በየቀኑ ለ10 ሰዓታት የሚቆይ ከፊል የተኩስ ማቆም ጀምሯል።

የጋዛ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እንደገለጸው፤ከጥቅምት 7 ጀምሮ ከ2 መቶ ሺህ በላይ ፍልስጤማውያን ተገድለዋል ወይም ቆስለዋል፤ይህም ከህዝቡ 10 በመቶውን ይሸፍናል።

ሀሚድ አብደላ

ሐምሌ 21/2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *