የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ የስድስተኛ ክፍል የሚኒስትሪ ፈተና ውጤት እስከ አርብ ድረስ ለተማሪዎች ገለፃ ይደረጋል ሲል አስታውቋል።
የቢሮው ምክትል ስራ አስኪያጅ ዶ/ር ካሳሁን ገላና በቅርቡ የስምንተኛ ክፍል የፈተና ውጤት ይፋ አድርገናል ያሉ ሲሆን ፤የስድሰተኛ ክፍል ፈተናም እርማቱ እየተጠናቀቀ በመሆኑ በዚህ ሳምንት ይፋ እናደርጋለን ሲሉ ለጣቢያችን ገልፀዋል።
በዘንድሮ አመት አጠቃላይ 488 ሺህ 458 የስምንተኛ ክፍል ተማሪዎች አስፈትነናል ያሉት ሃላፊው ከ50 በላይ በማምጣት ያለፉት ተማሪዎች 78.7 በመቶ ወይንም 384 ሺህ 498 የሚሆኑት ናቸው ብለዋል።
ዶ/ር ካሳሁን ለ2018 የትምህርት ዘመን የተጎዱ በተለይ የሃያስኩል ትምህርት ቤቶችን ግንባታ በመንግስትና በማህበረሰቡ አቅም ለመገንባት ስራዎች መጀመራቸውን ተናግረዋል።
መፀሃፍን በተመለከተ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመጽሐፍት እጥረት መኖሩን የገለፁት ሃላፊው፤የመጽሃፍት እጥረቱን ክፍተቱን ለመሙላት ወደ 29 ሚሊዮን መፅሃፍ ይታተማል ብለዋል።
ከዚህ ውስጥ 23 ሚሊዮን የሚሆነው በመንግሥት የሚታተም ነው ያሉ ሲሆን ቀሪዎቹ ወደ ስድስት ሚሊዮን የሚሆነው ደግሞ በልማት የርዳታ ድርጅቶች እንደሚታተሞ ጠቁመዋል።
ልኡል ወልዴ
ሐምሌ 22/2017 ዓ.ም
