ከግብር ክፍያ ጋር በተያያዘ ከ12 ሺህ በላይ ዉሳኔዎች ላይ ቅሬታ ቀርቧል ተባለ።

ከግብር ከፋዩች የቀረበ ከፍተኛ የግብር ክፍያ ዉሳኔ ቅሬታ 53 በመቶ ያህሉ ተገቢ ሆኖ መገኘቱንም ሰምተናል።

በባለፈዉ በጀት አመት ከኦዲት ጋር በተያያዘ ከ12 ሺህ በላይ ዉሳኔዎች ላይ ቅሬታ መቅረቡን የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ተናግሯል

የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተሩ አቶ ሰዉነት አየለ ከቀረቡት ቅሬታዎች ወደ 6 ሺህ ያህሉ ቅሬታዉ ተገቢነት ያለዉ ሆኖ መገኘቱን ገልፀዋል።

በዚህም ግብር ከፋዩ ባቀረበዉ ቅሬታ በኦዲተሩ የተሰጠዉ ዉሳኔ ትክክል አለመሆኑ ተጣርቶ 53 በመቶ ሊሻሻል ችሏል ሲሉ ዳይሬክተሩ አንስተዋል።

ከጣቢያችን ጋር ቆይታ ያደረጉት ዳይሬክተሩ ለቅሬታዎቹ 97 በመቶዉ ምላሽ የተሰጠበት መሆኑን ገልፀዋል።

ቢሮዉ በዘረጋዉ አሰራር የኦዲት ጥራት አረጋጋጭ የስራ ክፍል መቋቋሙን የተናገረ ሲሆን በኦዲተሮች የሚወሰን የግብር ክፍያ ዉሳኔ ምን ያህል ትክክለኛ ነዉ የሚለዉን የሚያጣራ ነዉ ተብሏል።

በግብር ከፋዩች ላይ ያለአግባብ ከፍተኛ የሆነ ግብር ተተምኖ ከሆነ በማጣራት ዉሳኔዉ ዉድቅ ሆኖ እንዲሻሻል እንደሚደረግ ተገልፆል።

የግብር ክፍያ ዉሳኔ ዙሪያ ግብር ከፋዩች ቅሬታቸዉን ከወረዳ ጀምሮ በየደረጃዉ ማቅረብ እንደሚችሉ ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።

ቁምነገር አየለ

ሐምሌ 23/2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *