ዩናይትድ ኪንግደም በመስከረም ወር ለፍልስጤም እውቅና ልትሰጥ ትችላለች አሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ

እስራኤል “በጋዛ ያለውን አስከፊ ሁኔታ ለማስቆም ተጨባጭ እርምጃዎችን” ካልወሰደች ዩናይትድ ኪንግደም በመስከረም ወር ለፍልስጤም እውቅና እንደምትሰጥ ጠቅላይ ሚኒስተር ኪር ስታርመር ተናገሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ እስራኤል የተኩስ አቁም ስምምነትን ማድረግ፣ የሁለት አገር መፍትሄ የሚያመጣ ዘላቂ ሰላም ማስፈን እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የእርዳታ አቅርቦቱን እንደገና እንዲጀምር መፍቀድን ጨምሮ፣ ሌሎች ቅድመ ሁኔታዎችን ማሟላት አለባት፤ አለዚያ እንግሊዝ እርምጃውን በመስከረሙ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ትወስዳለች ብለዋል።

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ እርምጃው “ለሐማስ አስከፊ አሸባሪነት ሽልማት ነው” ብለዋል።

የዩናይትድ ኪንግደም መንግሥት ከዚህ ቀደም ለፍልስጤም እውቅና መስጠት እንደ የሰላም ሂደት አካል ከፍተኛ ተጽዕኖ በሚያሳድርበት ጊዜ ሊደረግ ይገባል ሲል ተናግሯል።

ሆኖም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፍጥነት እርምጃ እንዲወስዱ ከራሳቸው የፓርላማ አባላት ጭምር ጫና እየደረሰባቸው ነው።

ሐምሌ 23/2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *