ከተላኩ የዘረመል ምርመራ ይደረግልኝ ጥያቄዎች ዉስጥ በፌደራል ጠቅላይ ፍርድቤት የህፃናት ፍትህ ፕሮጀክት ድጋፍ 70 ለሚሆኑት ምርመራው እንደተደረገ ተገልጿል ፡፡
የፕሮጀክቱ ዳይሬክተር ዳኛ ተክለ ሀይማኖት ዳኜ ከጣቢያችን ጋር ባደረጉት ቆይታ እንዳሉት በፍርድቤት ትእዛዝ በሚመጡ እና በአስገድዶ መድፈር በሚፈፀሙ የወንጀል ጉዳዮች ላይ በፖሊስ እና በአቃቤ ህግ ምርመራዎቹ ለፕሮጀክቱ እንደሚቀርቡ ገልፀዋል
በአመቱ ከተደረጉ የዘረመል ምርመራዎች ዉስጥ አብዛኞቹ ምርመራዎች አባትነት የተረጋገጠባቸዉ ናቸዉ ያሉት ዳኛ ተክለሃይማኖት ነገር ግን በምርመራ መረጋገጡ ብቻ በቂ ስለማይሆን የፍርድ ቤት ዉሳኔ ተጠባቂ ይሆናል ብለዋል
የበጀት እጥረት ትልቅ ፈተና እንደሆነ ያነሱት የፕሮጀክቱ ዳይሬክተር ያለዉን አመታዊ በጀት በመጠቀም እና አባትነታቸዉ የተረጋገጠ ጉዳዮችን ወጪዉ በአባት እንዲሸፈን በማድረግ እየተሰራ መሆኑን አንስተዋል ፡፡
ፕሮጀክቱ በህግ ስርአቱ በተከራካሪነት እና በተከሳሽነት አንዲሁም በተጠቂነት የሚያልፉ ህፃናትን ለመደገፍ የተቋቋመ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
አቤል እስጢፋኖስ
ሐምሌ 28/2017 ዓ.ም
