በመዲናዋ ከ80 ሺህ በላይ የከተማ ስደተኞች እንደሚገኙ ኢሰመኮ ገለፀ።

ከእዚህ ውስጥ ከፍተኛውን ቁጥር የሚይዙት ኤርትራውያን ናቸው ተብሏል።

73 ሺህ ከኤርትራ፣ ከ2 ሺህ 4መቶ በላይ ከየመን፣ ከሶማሊያ፣ ከደቡብ ሱዳን፣ከሶሪያ፣ ከኮንጎ እና ከሌሎች ሀገራት ተሰደው የመጡ መሆናቸዉን በሪፓሪቱ አመላክቷል።

ኮሚሽኑ ፤ የኢትዮጵያ መንግሥት ስደተኞችን በተለይም በሱዳን የሚካሄደውን ግጭት ሸሽተው ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ ስደተኞችን መቀበል እና ማስተናገዱን የቀጠለ መሆኑ በበጀት አመቱ ከታዩ ለውጦች መካከል ይጠቀሳሉ ብሏል።

በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ ስደተኞች የብሔራዊ መታወቂያ፣ የትምህርትና የጤና አገልግሎቶችን የሚያገኙበት ሁኔታ መመቻቸቱንም አስታዉቋል።

ስደተኞች በተለያዩ ሥራዎች ላይ በመሰማራት ራሳቸውን እና ቤተሰቦቻቸውን በኢኮኖሚ የሚደግፉበት ሁኔታ እና የስደተኞችን እና ጥገኝነት ጠያቂዎች የሥራ መብት የሚደነግግ መመሪያ መጽደቁም ተገልጿል።

እነዚህ በከተማ የሚገኙ ስደተኞች  በመንግሥት ዕቅድ ከመጠለያ ጣቢያ ውጭ እንዲኖሩ የተፈቀደላቸው በሚል ተለይተው የሚታወቁ ናቸው።

ምዝገባ ያልተደረገላቸው ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ጥገኝነት ጠያቂዎች በአዲስ አበባ ከተማ እንደሚገኙም ተገልጿል።

ሊዲያ ደሳለኝ

ሐምሌ 29/2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *